ጥቅሱ፥ የቱ ጋ ነው? 0 | ዲቮሽናል በሲር አይናለም By Seer Aynalem Mersie · June 20, 2026 አንድ \'አገልጋይ\' ማምሻውን በማህበራዊ ድረ-ገጽ በግንባር ቀርቦ፥ ሰዎችን ከሎሚ ጋር በማመሳሰል፦\"ከአንበሳ እኔ አለሁ፣ ከእሳትም እኔ አለሁ፣ ከውኃም እኔ አለሁ፤ ከሰዎች ግን ተጠበቁ\" የሚል ጥቅስ ተናግሯል። ጥቅሱን ከመጽሐፍ ሳላገኘው ሊነጋ ነው። ካገኛችሁት አትጨክኑብኝ። ጥቅሱ ከሌለ ግን ሎሚው ማን እንደሆነ ታውቋል።መልዕክቱን ማንበብ፣ ማጎልበት ወይም መተቸት ይገባል። ነገ በቀጣዩ መልዕክት እንገናኝ!! ሲር አይናለም መርሴ