እንዴት እንናገር?
ቴቴማናዊው ኤልፋዝ ኢዮብን "አንተም፥ እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን? እንዳያይ የጠቈረ ደመና ጋርዶታል...ብለሃል" ይለዋል (ኢዮብ 22፡13-14)።
ኢዮብ በእርግጥ እንዲህ ብሎ ከሆነ፥ መላ ምት ነው። መላ ምትና እንደ እግዚአብሔር ቃል የሚነገር ንግግር ከፍተኛ ልዩነት አላቸው። መጽሐፍ "ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር" ይላል (1ጴጥ 4:11)። እንደ ኢዮብ በስሜት እንደመጣልን መናገር እና እንደ እግዚአብሔር ቃል መናገር ውጤታቸው ይለያያል ፤በእርግጥ ስንፍና ካልሆነ "እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን? እንዳያይ የጠቈረ ደመና ጋርዶታል" ይባላልን? ቃሉ ምን ይላል? "እግዚአብሔር አዋቂ ነው።" (1 ሳሙ 2፡3)። " "በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነው" (2 ቆሮ 4:6)።
እንደመጣልን በስሜት አንናገር። ጸሎትም ቢሆን የሚሠራው እንደርሱ ቃል ሲሆን ነው።
መልዕክቱን ማንበብ፣ ማጎልበት ወይም መተቸት ይገባል። ነገ በቀጣዩ መልዕክት እንገናኝ!!

ሲር አይናለም መርሴ
በሲር አይናለም መርሴ የተጻፈውን ጅረት መጽሐፍ ከታች ያለውን በመጫን ያውርዱ Download the Book Jiret by Seer Aynalem Mersie Below.