የማህበራዊ ሚዲያ …ዎች ሰለቹን

የማህበራዊ ሚዲያ ...ዎች ሰለቹን

አንድ ሰው ወይም ማሕበረሰብ፥ ትንሽዬ አልያም ኃይል አልባ ከሆነ ንቀት ተጠናውቶታል። የበታችነት መንፈስም ያጠቃቸው አካላት መገለጫቸው ንቀት ነው። በየመስኩ ንቀት ተስፋፍቷል። በተለይ ደግሞ በአምልኮ ስፍራዎች እና በእምነት ተቋማት ያለው የንቀት ጥግ አይጣል ነው ፤ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው እና በማሕበራዊ ሕይወቱ ረገድ የተንሰራፋው የንቀት ጉድ፥የዕለት ተለት ትዕይንት
ስለሆነ የግድ መታደምና መኖር ከተጀመረ ሰነባበተ።

'አለው' የተባለው፥ የሌለውን መናቅ፣ 'ተሾመ' የተባለው፥ ጀሌውን መናቅ፣ 'መምህር' የተባለው፥ መዕመኑን መናቅ ፣ኃጥኡ ጻድቁን መናቅ፣ ሐሰተኛው፥ እውነተኛውን መናቅ ፣ አጭበርባሪው፥ ንጹኁን መናቅ፣ ሽብርተኛው፥ የዋሁን መናቅ፣ ሟርተኛው፥ ቅኑንና የዋሁን መናቅ፣ ያልተማረው፥ የተማረውን መናቅ፣ሕዝብ መናቅ፣ መሪን መናቅ፣ አገርን መናቅ፣ ጸጋን መናቅ፣ ወዘተ መናቅ።

መጽሐፍ ሲናገር "እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም፤" ይላል (ኢዮብ 36:5)። ማንንም የማይንቁ እነርሱ ኃያላን ናቸው። ንቀት የምናምንቴዎች መለያ ነው (1ሳሙ 10፡27)። "በንቀት የተጠመቁ ምናምንቴዎችን በቀላሉ ለማየት፥ እባክዎን ፌስቡክዎን ወይም የዩቲዩብ ቻናልዎን ይክፈቱ!"፥ ብዙ ተከታይ ያለው በንቀት ተሳዳቢ ሰው አላጋጠመዎትም? አሁንስ፥ እጅ እጅ አለን!


መልዕክቱን ማንበብ፣ ማጎልበት ወይም መተቸት ይገባል። ነገ በቀጣዩ መልዕክት እንገናኝ!!


ሲር አይናለም መርሴ


በሲር አይናለም መርሴ የተጻፈውን ጅረት መጽሐፍ ከታች ያለውን በመጫን ያውርዱ Download the Book Jiret by Seer Aynalem Mersie Below.

ለማውረድ
guest
0 አስተያየቶች
አዲሱ
የቆየው አብላጫ ድምፅ ያለው
የመስመር አስተያየቶች
ሁሉንም አስተያየቶች ለመመልከት