አሽቃባጭ አንፈልግም

አሽቃባጭ አንፈልግም

ኤሊሁ የተባለ የኢዮብ ወዳጅ "በዕድሜ ያረጁ ጠቢባን አይደሉም፥ሽማግሌዎችም ፍርድን አያስተውሉም" ሲል ይሞግታል (ኢዮብ 32፡9)።

ሰው እድሜው እየጨመረ ሲመጣ፣ ሲሸመግል፣ ልምድ ሲያካብት በሳል ሊሆን ይገባል። ብስለት ደግሞ ነገርን በመተው፣ይቅርታና ምህረትን በማድረግ፣ያለፈውን ነገር በመተው፣ እውነትና ጽድቀን በመኖር፣የቀደመውን ፍቅር ባለመተው፣ከልዩነት ይልቅ፥አንድነት ላይ በመስራት ነው።

አሁን አሁን የሚታየው ነገር፥ ኤሊሁ እንዳለው፥በሁሉም መስክ "እኛ እንቀድማለን" የሚሉና በጉዳዩ ላይ ያፈጁና ያረጁ፥ "ጠቢብ ነኝ" ይላሉ ነገር ግን ጥበብ የላቸውም። ይፈርዳሉ፥ ነገር ግን ፍርደ ገምድል ናቸው። ይሰብካሉ (ያስተምራሉ) ነገር ግን ኑሮአቸው አይመሰክርም።

በዚህ ዘመን አገርን ወደ መቀመቅ እየከተተ የመጣው ጉዳይ ቢኖር፥ ያረጀ ወይም የሸመገለ ፖለቲካ ወይም ኢኮኖሚ ወይም ማህበራዊ ሕይወት ወይንም ደግሞ እምነት (ኃይማኖት) ሳይሆን፥በመስኩ ላይ ተሰማርተው ከሚጠበቅባቸው ሥራና ፍሬ ይልቅ ወሬ እና አሉባልታ ያስረጃቸው(ያሸመገላቸው) ግለሰቦች ጉዳይ ነው። ቤት ይቁጠራቸው።

ጌታ እንደ ኤሊሁ ያለ፣የማያቆላምጥ እና የማያሽቃብጥ ብሎም ጽድቅን የሚኖር ሰው፥ በየመስኩ ይስጠን!!!

መልዕክቱን ማንበብ፣ ማጎልበት ወይም መተቸት ይገባል። ነገ በቀጣዩ መልዕክት እንገናኝ!!


ሲር አይናለም መርሴ


በሲር አይናለም መርሴ የተጻፈውን ጅረት መጽሐፍ ከታች ያለውን በመጫን ያውርዱ Download the Book Jiret by Seer Aynalem Mersie Below.

ለማውረድ
guest
0 አስተያየቶች
አዲሱ
የቆየው አብላጫ ድምፅ ያለው
የመስመር አስተያየቶች
ሁሉንም አስተያየቶች ለመመልከት