ተገደን፥ ዝም…ምምም
መጽሐፍ " ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም ፤እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል" ይላል። (ሮሜ 3:11)
ከላይ ያለው ጥቅስ አይደለም፤ሁላችንን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መስታዎት እንጂ። ጻድቅ ጠፋ፤ አስተዋይም አልተገኘም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ማግኘትማ ልክ ጤፍ በጨለማ ውስጥ እንደመልቀም ነው፤ሁሉ ስህተት ነው። ደርሶ 'የስህተት ትምህርት' በሚል ፈሊጥ አራሚ ለመሆን መውተርተር።
መግቢያው ላይ የተጠቀሰው ቃል ለሁሉም መስክ ነው። ፖለቲካው፣ ኢኮኖሚው፣ ማህበራዊ ህይወቱ፣ ሚዲያው ወዘተ ጽድቅን፣ ማስተዋልን፣ እግዚአብሔርን የሸሸ ነው።
አሁን አሁን፥ በውሸት አባት (ዲያብሎስ) የተመረቁ ውሸተኞች ፖለቲካውን፣ ኢኮኖሚውን፣ ማህበራዊ ህይወቱን፣ ሚዲያውን፣ እየተቆጣጠሩት ስለመጡ እውነተኞች ዝምታን መርጠዋል። "ኢዮብም ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና እነዚያ ሦስቱ ሰዎች መመለስን ተዉ።" እንዲል መጽሐፍ (ኢዮብ 32:1)።
ጌታ ኢየሱስ "እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤" ይላል (ዮሐ 14:6)። በእርግጥ እውነትን የሚፈልግ ሰው ካለ፥ እውነት የሆነውን ጌታ በእውነት ይከተል፥ "በጌታ ነኝ" እያለ ትውልድ የሚያደናግርም ወሮበላ። "ወሮበላ" የሚለውን ቃል፥ የሚተካ የተሻለ ቃል ሳገኝ እቀይረዋለሁ፥ እስከዛው ይቅርታ !!
መልዕክቱን ማንበብ፣ ማጎልበት ወይም መተቸት ይገባል። ነገ በቀጣዩ መልዕክት እንገናኝ!!

ሲር አይናለም መርሴ
በሲር አይናለም መርሴ የተጻፈውን ጅረት መጽሐፍ ከታች ያለውን በመጫን ያውርዱ Download the Book Jiret by Seer Aynalem Mersie Below.