ስምምነት፥ ሰላም፥ በጎነት

ስምምነት፥ ሰላም፥ በጎነት

ከእግዚአብሔር ጋር ያልተስማማ ሰው፣ ቡድን ወይም አገር መቼም ቢሆን ሰላም አይኖረውም፤ በጎነትንም በሕይወት ዘመኑ አያገኝም። ሰው ከሰው ጋር ሊስማማ ይሞክራል፣ ቡድን ከቡድን ጋር ለመስማማት በጠረጴዛ ዙሪያ ይቀመጣል፣አገር ከአገር ጋር ለመስማማት ቀጠሮ ይይዛል፣ ለስምምነት ሲባል የማይከፈል መስዋዕትነት የለም፥ ነገር ግን ዘለቄታ የለውም። ለምን? ምንድን ነው ችግሩ? የመጀመሪያው ስምምነት ከሰላሙ አለቃ ከእግዚአብሔር ጋር ካልሆነ መቼም ቢሆን ስምምነት የለም፥ ሰላምም ቢሆን በቀላሉ አይገኝም፣ በጎነትም ቢሆን ህልም ነው።

መጽሐፍ ይህንኑ ሲያረጋግጥ "አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፤ በዚያም በጎነት ታገኛለህ።" ይላል (ኢዮብ 22፡21)።

ስለዚህ ሰዎች፣ ልዩ ልዩ ቡድኖችም ሆናችሁ አገሮች መርሁን ተከተሉ። ቅድሚያ ስምምነት ከእግዚአብሔር ጋር። አለዚያ ዘመናችሁ ሁሉ ያለስምምነት፣ ያለ ሰላምና ያለበጎነት ያልቃል። ጌታ ማስተዋልን ይስጠን!!!

መልዕክቱን ማንበብ፣ ማጎልበት ወይም መተቸት ይገባል። ነገ በቀጣዩ መልዕክት እንገናኝ!!


ሲር አይናለም መርሴ


በሲር አይናለም መርሴ የተጻፈውን ጅረት መጽሐፍ ከታች ያለውን በመጫን ያውርዱ Download the Book Jiret by Seer Aynalem Mersie Below.

ለማውረድ
guest
0 አስተያየቶች
አዲሱ
የቆየው አብላጫ ድምፅ ያለው
የመስመር አስተያየቶች
ሁሉንም አስተያየቶች ለመመልከት